በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !

የኮቪድ ስርጭት በመቀነሱ ምክንያት ከዚህ  ቀደም በምዝገባ  ወደ  ቤተ  ክርስቲያን ይገባ  የነበረው  ሂደት  ከአርብ  ሐምሌ  16, 2013 ዓ/ም (July 23, 2021) ጀምሮ  ቅድሚያ  የመጣ  ምዕመን የተዘጋጀው ወንበር  እስኪ ሞላ  ድረስ ገበቶ  መንፈሳዊ  አገልግሎት ማግኘት   የሚችል  መሆኑን  ከወዲሁ  እያሳወቅን   ነገር ግን ቅዳሴ  ከተገባ  በኃላ የሚመጣዉን   ማንኛውንም ምዕመን  በቤተ ክርስቲያን  ስርዓት  መሠረት  ከውጪ ሆኖ ማስቀደስ የሚችል መሆኑን ከወዲሁ  በእግዚአብሔር  ስም   በአክብሮት  እናሳውቃለን:: የክርስትና አገልግሎት ከፈለጉ እባክዎን ይህንን ቅጽ ይሙሉ የክርስትና አገልግሎት መጠየቂያ ቅጽ

"ወትባርክ አክሊለ ዓመተ ምሕረትከ" | "በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ"--መዝ.64፤11።

የዕለት፣ የዓመት፣ የዘመናት ጌታ እንደ ኃጢአታች ብዛት ሳይሆን እንደ ምሕረቱ ብዛት ዘመነ ማቴዎሰን በሰላም አሳልፎ ወደ ዘመነ ማርቆስ እንኳን በሰላም አሸጋገረን።ዘመኑን ዋጁ እንደተባለ ዘመነ ማርቆስን የፍቅር ፣የዕረቅ፤ የመተሳሰብ ወደ እግዚአብሔር የምንመለስበት የንስሃን መንገድ የምንይዝበት እንዲሆን እግዚአብሔር ይርዳን ።።

መልአከ አርአያም ብርሃኑ ጎበና

ጾመ ፍልሰታ 2/3

ቅዱስ ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ወደ እየሩሳሌም ሲመጣ ያገኛታል በዚህ ጊዜ ትንሳኤዋን ሌሎች ሐዋርያቶች አይተው ለእሱ የቀረበት መስሎት ተናዶ በፊት የልጅሽን ትንሳኤ ሳላይ ቀረው አሁን ደግሞ የአንቺን ትንሳኤ ሳላይ ቀርቼ ነበር ብሎ ከደመና ሊወረወር ቃጣው በዚህ ጊዜ እመቤታችን ቶማስን አፅናንታ ከእሱ በቀር ሌላ ትንሰኤዋን እንዳላየ ነገረችው።

ቶማስም ሐዋርያት ወዳሉበት እየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ እመቤታችንን ቀበርናት ብለው ነገሩት እሱም አውቆ ምስጥሩን ደብቆ አይደረግም ሞት በጥር በነሀሴ መቃብር አላቸው ለማሳየትም መቃብር ሲከፍቱ አጧት በዚህ ጊዜ"እመቤታችን ተነስታ አርጋለች ብሎ ሁኔታውን ተረከላቸው ለምስክርም ይሆናል ብሎ የሰጠችውን (ሰበኗን) አሳያቸው ሰበኗንም ለበረከት ቆራርጠው ተከፋፍለው ወደ ሀገረ ስብከት ተበታትነዋል።

ጾመ ፍልሰታ 3/3

በዓመቱ ትንሳዬሽን ቶማስ አይቶ እንዴት እኛ ይቅርብን ብለው ከነሀሴ 1 ጀምሮ ሱባዬ ገቡ በነሀሴ14ቀንም ትኩስ በድን አድርጕ አምጥቶ ሰጣቸው ከቀበሯትም በጟላ በነሀሴ16 ተነስታለች በዚህ ቀን ጌታ ቀድሶ እመቤታችንም በልጇ እጅ ቆርባለች ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የሐዋርያት ቤተክርስትያን የእመቤታችንን በረከት ለማግኘት ይህች ጊዜ ትፆማለች። የእመቤታችን በረከቷ አማላጅነቷ ከሁላችንም ጋር ይሁን እናትነቷ ይብዛብን አሜን አሜን አሜን መልከም የፍልሰታ ፆም ይሁንልን ሀገራችንን ሰላም ታድርግልን አሜን ።

<<< ወስብሀት ለ እግዚአብሔር >>>
<< ወለ ወላዲቱ ድንግል >>
<< ወለ መስቀሉ ክቡር >>