እባክዎ የሚከተሉትን እንዲያነቡ እና ተግባራዊ እንዲያደርጉ  በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን::

በCOVID-19 ወረርሽኝ ወቅት የተደረጉ ለውጦች

  • ማንኛውም አይነት ህመም የበሽታ ምልክት ከታየቦት ወደ ቤተ ክርስቲያን አይምጡ::
  • ወደ ቤተ ክርስቲያን ቅጥር  ጊቢ  ውስጥ ከገቡበት  ግዜ  ጀምሮ አፍንጫ እና አፍን ሁል ጊዜ በጭምብል መሸፈን አይርሱ::
  • ወደ ውስጥ ከመግባትዎ በፊት  የሙቀት  መጠንዎን   ስንለካ ከ100 ℉ በላይ  ከሆኑ  እንዲመለሱ እንጠይቆታለን::
  • ወደ ቤተ  ክርስቲያን  ከመግባዎ  በፊት  በር  ላይ  በተዘጋጀው  የእጅ  አልኮል ተጠቅመው  እጅዎትን  ያፅዱ:: እንደገና ወጥተው ከተመለሱ ፤ እጅዎትን ዳግም  ያፅዱ ::
  • ወደ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሲገቡ  የእጅ ጓንት  አድርገው  ከሆነ  ያውልቁት::
  • ወደ ቤተ  ክርሲቲያን  ሲገቡ  ለጫማዎ  መያዣነት  የተጠቀሙበትን  ፌስታል ሲወጡ ወስደው  ይጣሉት::
  • ለአገልግሎት የተዘጋጁ  የመቀመጫ  ወንበሮችን  ከቦታቸው  አያንቀሳቅሷቸው::
  • ሲገቡ ወይም ሲወጡ 6 ጫማ ርቀትዎን ጠብቀው ይሁን፡፡

የሁል ጊዜ የቤተክርስቲያን ደንቦች

  • ቤተ ክርሲቲያን ውስጥ ከገቡ በኋላ አስገዳጅ ነገር ካልተፈጠረ በስተቀር መንቀሳቀስ ፈፅሞ የተከለከለ ነው::

ስጋወደሙን ለመቀበል

  • መጀመሪያ በCovid19 ወረርሽኝ ወቅት የተደረጉ ለውጦችን ከላይ ይመልከቱ::
  • እባኮትን ቅዳሴ  ከመገባቱ  ቀደም  ብለው  ቤተ  ክርስቲያን  6AM  ላይ  ይድረሱ :: ነገር ግን  ህፃን  ልጅዎን  የሚያቆርቡ  ከሆነ ፤6:30AM ይድረሱ  አርፍደው  ቢመጡ  በር  ላይ  ያሉ  አገልጋዮች  ስለማያስገቦት   መርፈዶን  ካወቁ   አይምጡ፡፡  ሌላ  ጊዜ  ቀደም  ብለው ይምጡ::

ክርስትና ለማስነሳት

  • መጀመሪያ በCovid19 ወረርሽኝ ወቅት የተደረጉ ለውጦችን ከላይ ይመልከቱ::
  • ክርስትና ከመጀመሩ በፊት ቀደም ብለው  ከቤተ  ክርስቲያን 4:50AM  ይድረሱ። ክርስቲናው  የሚጀመረው  5፡00AM  ነዉና ፤ አርፍደው  ቢመጡ  ሙሉ  የክርስቲና  ስርዓቱን  ስለማያገኙ  እባኮን  በሰዓቱ  ይድረሱ::
  • ወደ ቤተ  ክርስቲያን  ቅጥር  ጊቢ  ውስጥ   ከገቡበት  ግዜ  ጀምሮ  የአፍና  አፍንጫ  ጭምብል  በአግባቡ ይጠቀሙ ::
  • ልጅዎን ክርስትና  ከማስነሳትዎ  በፊት  በቤተ  ክርስቲያን  ስርዓት  መሠረት  የህፃንዎን  ፀጉር  ይላጩት፡፡  ነገር  ግን  መላጨት ካላመቾት  የልጅዎን ፀጉር ያሳጥሩ፡፡
  • በቤተ ክርስቲያን ስርዓት  መሠረት  ህፃንዎ  እስከሚጠመቅ  ድረስ  ደጋግመው  ያጥቡት፡፡  ነገር  ግን  ከተጠመቀ  በሀላ   ስጋወደሙን  እስኪቀበል  ድረስ  እንዳያጠቡት::
  • የክርስትና  ስም በሚወጣበት ጊዚ የልጅዎን የክርሰትና  ስም   ተከታትለዉ ያዳመጡ እና ያስታዉሱ፡፡
  • የክርስትና ምስክር  ወረቀት   ለማግኘት  ልጅዎ  ክርስትና  ከተነሳ  በኋላ  የሚላክሎትን  ኢሜል   ከፍተው መጠይቆቹን  በአማረኛ  እና  በእንግልዘኛ  በጥንቃቄ   ሁሉንም     ሞልተው  Submit  ያድርጉ :፡
  • የክርስትናው ስነ ስርዓት  በሚካሄድበት  ወቅት  ርቀትዎን  ጠብቀው  መቆሞን  እንዳይረሱ።  ከተፈቀደሎት  ስፍራ  ውጭ  ተንቀሳቅሶ  ፎቶ  ማንሳት  በጥብቅ  የተከለከለ ነው::
በቤተክርስቲያኗ  በሚሰጡ የተለያዩ አገልግሎቶች የበኩልዎን ተሳትፎ ለማበርከት ይህንን ቁልፍ በመጫን ያመልክቱ::