የኆኅተ ምሥራቅ ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን አመሰራረት

Believing in God’s Word and Spirit
የኆኅተ ምሥራቅ ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን በጥቅምት 1 ቀን 2004 ዓ.ም (November 9, 2011) በሲልቨር ሰፕሪንግ ሜሪላንድ: አድራሻው 8900 Georgia Ave, Silver Spring, MD 20901 ንብረትነቱ የሌሎች ቤተ እምነት በሆነው ሕንጻ አዳራሽን በመከራየት፤ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ መምህራን፣ ዘማሪያን፣ የሰንበት ት/ቤት አባላት እንዲሁም ምዕመናን እና ምዕመናት በተገኙበት በብፁዕ አቡነ አብርሃም ቡራኬ ተመሰረተ።
ቀድሞ በቨርጂንያ ግዛት በሀገረ ስብከቱ ሥር ተተክሎ ከነበረው የምሥራቀ ፀሓይ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የሰበካ ጉባኤ አስተዳደር ጋር በመመካከር በአገልጋይ ካህናትም ሆነ በምእመናን ዘንድ ቅሬታ ሳይፈጠር የአገልጋይ ካህናት እጥረት ስለነበር የአገልግሎት ክፍተት እንዳይፈጠር በማሰብ ያሉትን ካህናት በአግባቡ ለመጠቀም የኆኅተ ምሥራቅ ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ቅዳሜ እንዲሆን ተደረገ።

ወቅታዊ መልእክት

“ሕዝቤ ሆይ፥ ና ወደ ቤትህም ግባ፥ ደጅህን በኋላህ ዝጋ ቍጣ እስኪያልፍ ድረስ ጥቂት ጊዜ ተሸሸግ።” ትንቢተ ኢሳይያስ 26 ፤ 20

ውድ የክርስቶስ ቤተሰቦች ምዕመናን “በመጨረሻው ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ ይህን እወቅ” ብሎ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለቅዱስ ጢሞቲዎስ እንደተናገረው እነሆ ዛሬ በዘመናችን መላው ዓለም በጭንቀት ማዕበል ተውጦ ይገኛል፡፡ ዳሩ ግን ክርስትያኖች እንደመሆናችን “እግዚአብሔር ከክፉ ሁሉ ይጠብቅሃል ፥ ነፍስህንም ይጠብቃታል፡፡” ተብሎ በቅዱስ ዳዊት እንደተነገረው መዝሙር 120፥6፡፡ ተስፋችን የሆነው አምላካችን እግዚአብሔር ዓለምን እያስጨነቀ ካለው ክፉ ደዌ እንደሚጠብቀንም ልናምን ይገባል፡፡ ተስፋ እንደሌላቸው እንደ አህዛብ ልንሸበር አይገባም ፤ ዳሩ ግን ከጸሎት ጋር ልናደርገው የሚገባውን ማንኛውንም ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ “ጥንቃቄ ይጠብቅሃል፥ ማስተዋልም ይጋርድሃል” መጽሐፈ ምሳሌ 2፥11 ፡፡ ተብሎ እንደተገለጸው ልናደርገው የሚገባውን ማንኛውንም ጥንቃቄ በግብዝነት ወይንም በስንፍና ሳናደርግ ቀርተን መከራ ቢመጣብንና እግዚአብሔርን ብናማርር የሚፈይደው ፋይዳ የለም፡፡
የኮሮና ቫይረስ የስርጭት አድማሱን እያሰፋ በመምጣቱ የቫይረሱን መዛመት ለመግታት በመንግስት በኩል እየተወሰዱት ካሉት እርምጃዎች አንዱ በስብሰባዎች ላይ የተሰብሳቢዎችን ቁጥር መገደብ ነው፡፡ በዚህ መሰረት የሜሪላንድ አገረ ገዢ እጅግ አነስተኛ ቁጥር ያለው ስብስብ ብቻ እንዲደረግ ያሳሰቡ ሲሆን ይህን ተላልፎ መገኘት እርምጃ የሚያስወስድ መሆኑን ተገልጿል ፡፡ ስለሆነም እገዳው በአዋጅ እስከሚነሳ ድረስ ምእመናን በቤታችሁ ሆናችሁ እንድትጸልዩና በካህናቱ መሪነት የሚደርሰውን የረቡዕና የአርብ የሰርክ ምህላና ጸሎት (6:30 am to 8:00 am) ፥ የእሁድ ቅዳሴ በኦንላየን (Online) እንድትከታትሉ እናስገነዝባለን፡፡ “ቍጣ እስኪያልፍ ድረስ ጥቂት ጊዜ ተሸሸግ” እንደተባለ ሁላችሁም በቤት ሆናችሁ መልካሙን ዘመን አምላካችን እንዲያመጣልን እንድትጸልዩ እናሳስባለን ፡፡ እግዚአብሔር በጎውን ዘመን ያምጣልን፡፡

Our Causes

Let Us Do Good

የአገልግሎት ተሳታፊ ለመሆን ከዚህ በታች ያለውን ቁልፍ በመጫን ይመዝገቡ

Latest News

Guiding Words for Living

ICON