እባክዎ የሚከተሉትን እንዲያነቡ እና ተግባራዊ እንዲያደርጉ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን::
በCOVID-19 ወረርሽኝ ወቅት የተደረጉ ለውጦች
- ማንኛውም አይነት ህመም የበሽታ ምልክት ከታየቦት ወደ ቤተ ክርስቲያን አይምጡ::
- ወደ ቤተ ክርስቲያን ቅጥር ጊቢ ውስጥ ከገቡበት ግዜ ጀምሮ አፍንጫ እና አፍን ሁል ጊዜ በጭምብል መሸፈን አይርሱ::
- ወደ ውስጥ ከመግባትዎ በፊት የሙቀት መጠንዎን ስንለካ ከ100 ℉ በላይ ከሆኑ እንዲመለሱ እንጠይቆታለን::
- ወደ ቤተ ክርስቲያን ከመግባዎ በፊት በር ላይ በተዘጋጀው የእጅ አልኮል ተጠቅመው እጅዎትን ያፅዱ:: እንደገና ወጥተው ከተመለሱ ፤ እጅዎትን ዳግም ያፅዱ ::
- ወደ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሲገቡ የእጅ ጓንት አድርገው ከሆነ ያውልቁት::
- ወደ ቤተ ክርሲቲያን ሲገቡ ለጫማዎ መያዣነት የተጠቀሙበትን ፌስታል ሲወጡ ወስደው ይጣሉት::
- ለአገልግሎት የተዘጋጁ የመቀመጫ ወንበሮችን ከቦታቸው አያንቀሳቅሷቸው::
- ሲገቡ ወይም ሲወጡ 6 ጫማ ርቀትዎን ጠብቀው ይሁን፡፡
የሁል ጊዜ የቤተክርስቲያን ደንቦች
- ቤተ ክርሲቲያን ውስጥ ከገቡ በኋላ አስገዳጅ ነገር ካልተፈጠረ በስተቀር መንቀሳቀስ ፈፅሞ የተከለከለ ነው::
ስጋወደሙን ለመቀበል
- መጀመሪያ በCovid19 ወረርሽኝ ወቅት የተደረጉ ለውጦችን ከላይ ይመልከቱ::
- እባኮትን ቅዳሴ ከመገባቱ ቀደም ብለው ቤተ ክርስቲያን 6AM ላይ ይድረሱ :: ነገር ግን ህፃን ልጅዎን የሚያቆርቡ ከሆነ ፤6:30AM ይድረሱ አርፍደው ቢመጡ በር ላይ ያሉ አገልጋዮች ስለማያስገቦት መርፈዶን ካወቁ አይምጡ፡፡ ሌላ ጊዜ ቀደም ብለው ይምጡ::
ክርስትና ለማስነሳት
- መጀመሪያ በCovid19 ወረርሽኝ ወቅት የተደረጉ ለውጦችን ከላይ ይመልከቱ::
- ክርስትና ከመጀመሩ በፊት ቀደም ብለው ከቤተ ክርስቲያን 4:50AM ይድረሱ። ክርስቲናው የሚጀመረው 5፡00AM ነዉና ፤ አርፍደው ቢመጡ ሙሉ የክርስቲና ስርዓቱን ስለማያገኙ እባኮን በሰዓቱ ይድረሱ::
- ወደ ቤተ ክርስቲያን ቅጥር ጊቢ ውስጥ ከገቡበት ግዜ ጀምሮ የአፍና አፍንጫ ጭምብል በአግባቡ ይጠቀሙ ::
- ልጅዎን ክርስትና ከማስነሳትዎ በፊት በቤተ ክርስቲያን ስርዓት መሠረት የህፃንዎን ፀጉር ይላጩት፡፡ ነገር ግን መላጨት ካላመቾት የልጅዎን ፀጉር ያሳጥሩ፡፡
- በቤተ ክርስቲያን ስርዓት መሠረት ህፃንዎ እስከሚጠመቅ ድረስ ደጋግመው ያጥቡት፡፡ ነገር ግን ከተጠመቀ በሀላ ስጋወደሙን እስኪቀበል ድረስ እንዳያጠቡት::
- የክርስትና ስም በሚወጣበት ጊዚ የልጅዎን የክርሰትና ስም ተከታትለዉ ያዳመጡ እና ያስታዉሱ፡፡
- የክርስትና ምስክር ወረቀት ለማግኘት ልጅዎ ክርስትና ከተነሳ በኋላ የሚላክሎትን ኢሜል ከፍተው መጠይቆቹን በአማረኛ እና በእንግልዘኛ በጥንቃቄ ሁሉንም ሞልተው Submit ያድርጉ :፡
- የክርስትናው ስነ ስርዓት በሚካሄድበት ወቅት ርቀትዎን ጠብቀው መቆሞን እንዳይረሱ። ከተፈቀደሎት ስፍራ ውጭ ተንቀሳቅሶ ፎቶ ማንሳት በጥብቅ የተከለከለ ነው::