የኆኅተ ምሥራቅ ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን አመሰራረት

Believing in God’s Word and Spirit
የኆኅተ ምሥራቅ ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን በጥቅምት 1 ቀን 2004 ዓ.ም (November 9, 2011) በሲልቨር ሰፕሪንግ ሜሪላንድ: አድራሻው 8900 Georgia Ave, Silver Spring, MD 20901 ንብረትነቱ የሌሎች ቤተ እምነት በሆነው ሕንጻ አዳራሽን በመከራየት፤ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ መምህራን፣ ዘማሪያን፣ የሰንበት ት/ቤት አባላት እንዲሁም ምዕመናን እና ምዕመናት በተገኙበት በብፁዕ አቡነ አብርሃም ቡራኬ ተመሰረተ።
ቀድሞ በቨርጂንያ ግዛት በሀገረ ስብከቱ ሥር ተተክሎ ከነበረው የምሥራቀ ፀሓይ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የሰበካ ጉባኤ አስተዳደር ጋር በመመካከር በአገልጋይ ካህናትም ሆነ በምእመናን ዘንድ ቅሬታ ሳይፈጠር የአገልጋይ ካህናት እጥረት ስለነበር የአገልግሎት ክፍተት እንዳይፈጠር በማሰብ ያሉትን ካህናት በአግባቡ ለመጠቀም የኆኅተ ምሥራቅ ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ቅዳሜ እንዲሆን ተደረገ።

ወቅታዊ መልእክት

እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ!

“ወሕዝብኒ ዘይነብሩ ውስተ ጽልመት ርእዩ ብርሃነ ዐቢየ ወለእለ ይነብሩ ውስተ ጽልመት ወጽላሎተ ሞት ብርሃን በርሀ ላዕሌሆሙ።” ትን.ኢሳ.9፤2።

“በጨለማ የሄደ ሕዝብ ታላቅ ብርሃን አየ ፤በሞት ጥላና በጨለማ ሀገርም ለነበሩ ብርሃን ወጣላቸው”

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

ቅድመ ልደተ ክርስቶስ የነበረው ዘመን የጨለማ ዘመን ነበረ ሲባል ፀሐይ ብርሃንዋን የነሳችበትና ምድሪቱ በጨለማ የተዋጠችበት ዘመን ነበር ማለት አይደለም በጨለማ የተመሰለ ኃጢአት የሰፈነበት፣ አለማወቅ ወይም ድንቁርና በሰው ላይ የነገሰበት ዘምን መሆኑን ለማመልከት ነው። “ሰው ግን ክቡር ሲሆን አላወቀም።ልብ እንደሌላቸው እንስሶችም ሆነ፣መሰላቸውም” እንዳለ ቅዱስ ዳዊት ።መዝ.49፤20። መላው የአዳም ዘርን ዲያብሎስ የላሜ ልጅ የአውራዬ ውላጅ ብሎ በሥጋ በነፍስ ተቆራኝቶት ይኖር ስለነበር አብዛኛውን አእምሮውን ለብዎውን ተነስቶ ዕደ ኅሊናው፣ እግረ ኅሊናው በድንቁርና ተገርኝቶ የአምላኩ ገጽታ ጠፍቶበት በተፈጥሮ ከእርሱ ያነሱትን ለእርሱ የተፈጠሩትን ፍጥረታት አምላኩ አድርጎ ያመለከበት የሰገደበት ኅሊናው በክህደት ጨላማ ተውጦ ለጣዖት የተገዛበት ወቅት ነበር። ይህን ጊዜ ነው አማናዊው ፀሐይ ኢየሱስ ክርስቶስ ኆኅተ ምሥራቅ ከተባለች ከድንግል ማርያም ተወልዶ ጨለማ ለዋጠው ዓለም ያበራው

 

ይህን ጊዜ ነው አማናዊው ፀሐይ ኢየሱስ ክርስቶስ ኆኅተ ምሥራቅ ከተባለች ከድንግል ማርያም ተወልዶ ጨለማ ለዋጠው ዓለም ያበራው “በጨለማ የሄደ ሕዝብ ታላቅ ብርሃን አየ ፤በሞት ጥላና በጨለማ ሀገርም ለነበሩ ብርሃን ወጣላቸው” ተብሎ አስቀድሞ  ነቢየ ልዑል በኢሳይያስ የተነገረው ቃለ ትንቢት ፍጻሜ ያገኘው። በዚህ በልደት ቀን ሰማያውያን መላእክት ከምድራውያን እረኞች ጋር በአንድነት ዘመሩ የጥበብ ሰዎች ጥበብን ያዩ ዘንድ ከምሥራቅ በኮከብ እየተመሩ ጥበብ በአካለ ሥጋ በተገለጸባት ቤተ ልሔም ተገኙ፤ይህ ሁሉ ሲሆን ሄሮድስና የመሲሁን መምጣት፣ የብርሃንን መገለጥ በጉጉት ሲጠባበቁ የነበሩ መምህራነ እስራኤል በታላቅ እንቅልፍ ውስጥ ነበሩ። ሰማያውያኑን ከምድራውያኑ ጋር በአንድነት ያስፈነደቀው ፤የምድር ነገሥታትን ወደ ምድረ ፍልስጤም እንዲመጡ ያስገደዳቸው ዐቢይ ክስተት መከሰቱን አንዳችም ነገር አያውቁም ነበር።

Our Causes

Let Us Do Good

የአገልግሎት ተሳታፊ ለመሆን ከዚህ በታች ያለውን ቁልፍ በመጫን ይመዝገቡ

Latest News

Guiding Words for Living

ICON